የፋይናንስ ቢሮ የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀምንና የ2016 ዕቅድ ገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ  የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ከተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ጋር ገመገመ፡፡  የተቋሙ አፈፃፀም ሪፖርት በዕቅድና በጀት ዝግጅት ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ሽመልስ ደምሴ በበጀት ዓመቱ ታቅደው የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት ግቦችና አፈፃፀም የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ  ቀርቧል፡፡

በቀረበው ዕቅድና አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከበጀት አስተዳደር፣ ከገቢ፣ ከመንግስት ፕሮጀክቶች፣ ከመንግስት ፋይናንስ፣ ከቤት ግብር፣ ከመንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከውስጥ ኦዲት፣ ከፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እና ከግዥ አንፃር በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ  የፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ  አቶ ግርማ ጊዲ በውይይቱ ማጠቃለያ እንዳሉት ቢሮው   የአስተዳደሩን ውስን ሃብት በቁጠባና ውጤታማነትን በማረጋጥ  በጠንካራ የአመራር ስርዓት እየተመራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የፈፃሚውና የሠራተኛው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ግርማ በቀጣይ  2016 በጀት ዓመት አመራሩና ሰራተኛው  በቅንጅት በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አሳስበዋል፡፡

Scroll to Top