ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ከሰራተኛዉ ጋር ገመገመ፡፡/The office reviewed the 2015 fiscal year performance report with the staff.

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ረዳት አቶ ፍቀዱ ኃይለጊዮርጊስ እንደገለፁት  የዕቅድ አፈፃፀሙ  ስንገመግም  እኛ የሰራነዉ ስራ ምን ዉጤት አመጣ ምንስ ክፍተቶች አሉብን ብለን  ለቀጣይ 2016 ለማረም በደንብ  ያመጣነዉን ዉጤት የበለጠ በማጠናከር የምንዘጋጅበት መሆኑን ጠቁመው ክፍተቶቻችንን አይተን በቀጣይ ዓመት እንዳይደገም የምናደርግበት ስለሆነ ሁላችንም ተገቢዉን ግምገማ ማድረግ አለብን ብለዋል።
 
የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገቢን ከማበልጸግና ፍትሃዊ የሃብት አመዳደብ ከማሳደግ አንጻር የተለያዩ ጥናቶች እና የአሰራር ስርአቶችን ውጤት ማምጣታቸው፣ ።የካፒታል ወጪን አፈጻጸም እያደገ መምጣቱ፣ የተጠናከረ የፋይናንስ እና የበጀት ዘርፍ ስልጠናዎች መሰጠት መቻሉን የእቅድና በጀት ዝግጅት ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ደምሴ በሪፖርቱ አቅርዋል፡፡

 ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማጎልበት ክፍተቶች እንዳይደገሙ በማረምና በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻለ ሰራ ማከናወን እንደሚጠበቅ   ዳይሬክተሩ በሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡

Scroll to Top