ቢሮው የ2016 ረቂቅ በጀት  የከተማዋን  የኢኮኖሚ  ዕድገት ለማስቀጠል እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የ2016 ረቂቅ በጀትን  ከምክር ቤት የመንግስት በጀት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሄደ።

 በረቂቅ በጀቱ፣ የበጀት ድልድል ድርሻ በመቶኛ ለካፒታል 57 ፐርሰንት 43 ፐርሰንት ሆኖ ቀርቧል።

 የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን እንደገለፁት ረቂቅ በጀቱ የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ከተያዘው ረቂቅ በጀት ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያነት የሚውል የካፒታል በጀት መሆኑን  ገልፀው ረቂቅ በጀቱ በከተማ አስተዳደሩ የተቀመጡ የልማት ግቦችን ትኩረት ለተሰጣቸው በተለይም ለትምህርት፣ ለውሃ፣ ለመንገድ፣ ለትራንስፖርት፣ ለጤና እና ለሌሎችም ፕሮጀክቶች በልዩ ትኩረት  እንደሚሰጠው ኃላፊው ገልፀዋል።
የመንግስት በጀት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ  ኮሚቴ  የከተማውን ነዋሪ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች የበለጠ ትኩረት መሰጠት እንዳለበትና የመሰረተ ልማት፣ የመኖሪያ ቤት፣ የጤና እና ዘላቂ ልማት ተግባራትን በተመለከተ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ  ጠቁመው በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ያላቸውን አስተያየትና ጥያቄዎች አቅርበዋል።
የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊዎችም ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

Scroll to Top