የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ  ልማት ቢሮና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ የ2016 በጀት ሰሚ ተደረገ፡፡

በጀት ሲዘጋጅ የበጀት ሥርዓቱን ጠብቆ በማዘጋጀት ገቢን ማሳደግና ወጪን መቀነስ ላይ መሰራት አንዳለበት የበጀት ሰሚ ፕሮግራሙን የመሩት የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬዲዋን ገልፀዋል፡፡
በውይይቱ መስሪያ ቤቶች የበጀት ዕቅዳቸውን ሲያቀርቡ የከተማ አስተዳደሩ ገቢ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት ተናግረው በጀት መደልደል ያለበት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በተሰጣቸው ጣሪያ ልክ አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ ተግባራትን በቅደም ተከተል ማከናወን እንዳለባቸው አሳስዋል፡፡

በተመሳሳይም ምርታማነት ማሻሻያ ማዕከል፣ ኮልፌ፣ የካ፣ አዲስ ከተማ ኢንዱስትሪል ኮሌጅ፣ አቃቂና ምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና ወጣቶች ስፖርት ቢሮ የ2016በጀት ዕቅዳቸውን አቅርበው መገምገሙ ተገልጿል፡፡

Scroll to Top