መሰረታዊና ፍትሃዊ አገልግሎት ለሁሉ አቀፍ ፕሮግራም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።/It was stated that basic and fair service is important for the universal program.

ዜጎች ከመንግስት ጋር በመሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን እና ተደራሽነትን ማሳደግ ይገባቸዋል ተባለ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የቻናል አንድ ማስተባበሪያ ለክፍለ  ከተሞች ፋይናንስ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ወጪና በጀት ቁጥጥር አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የህዝብ አቤቱታ እና ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎች፣ ለትምህርትና ጤና ቢሮ፣ ለዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ለተዉጣጡ ሃላፊ እና ተወካዮች በማህበራዊ ተጠያቂነት ፅንሰ ሃሳብ፣ በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እና በቅሬታና አቤቱታ አፈታት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ፕሮግራሙ አንድ ቅርፅ ይዞ መዋቅራዊ በሆነ መልኩ ተናበዉ እንዲሰሩ ለማስቻል የሚረዳ ተመሳሳይና ተመጋጋቢ ስራዎች በመሆናቸዉ ትስስር ማስፈለጉን የጠቀሱት የፋይናንስ ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች   አስተባባሪ አቶ አብይ ቢተው ናቸዉ።
የአገልግሎት አሰጣጥ ግምገማዉ በዋናነት ትኩረት ያደረገዉ የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነት ፣ ጥራት፣ ዉጤታማነት፣ ፍትሃዊነት እና ምላሽ ሰጪነት ላይ  በአገልግሎት ማሻሻያ ድርጊት መርሃ ግብር በመተግበር እንደሆነ የፋይናንስ ቢሮ ማህበራዊ ተጠያቂነት ተጠሪ አቶ ደሊል ሙዘይን ተናግረዋል።

Scroll to Top